Friday, August 6, 2010

Ewnetu Tekeste: Yeleban Tebeqa Adebalqeh Wuqa

’’የሌባን ጠበቃ አደባልቀህ ውቃ’’

ከቀጣፊውና ከሐሰተኛው ሳይሆን

ከእውነተኛው ከእውነቱ ተከስተ

እውነትን ሺህ ጊዜ ዘላብደው ለመቀየር ቢሞክሩ ከቦታዋ ጥቂት ፈቀቅ ማድረግ አይቻልም ፡፡’’እውነትን እውነት ያወጣዋል’’ ይላሉ አባቶች ምን ጊዜም ቢሆን በሐሰት ቢሸፍኗትም መገለጧና ውሸተኛውን ማዋረዷ አይቀርም ፡፡ የዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነው ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል ‘’የሸማቂ ብፁዕ የለውም’’ በሚል ርዕስ ጁላይ ቀን ሺህ ያቀረቡትን ጽሁፍ መነሻ በማድረግ ከጽሁፉ በስተግርጌ ከአንባብያን ከቀረቡ አስተያየቶች በተለይ በተራ ቁጥር በተጻፈ ‘’የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ያስለፈልፈዋል’’ እንደሚባለው ከቀረበው ከዲያቆኑ አርእስት ጋር የማይዛመድ ‘’ጥንቸል ወደዚህ ቅዝምዝም ወደዚያ’’ በሆነ በሐሰት ጽሁፍ በመቀበጣጠርና የሰውን ስም በመስረቅና ስም በማጥፋት ‘’ከእውነቱ ተከስተ’’ ብሎ በሰው ስም ሐሰት መጻፍና መጠቀም በጣም አስነዋሪና ቅጥፈትን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታውት ነው ፡፡

በየድህረ ገጹ የሚቀርቡ ጽሁፎች እውነትን የተመረኮዙና የመማሪያ አምዶች እንጂ በተለይ የእንደዚህ ዓይነቶቹ በነገር የሰከሩ የስም ሌቦች መጫወቻ መሆን አይገባውም ፡፡ ታዲያ ‘’የሌባን ጠበቃ አደባልቀህ ውቃ’’ ነውና ዥብን ከነ ቦጫቂ ግልገሎቹ አደባልቆ መዉቃት የማያወላውል መፍትሄ ስለሆነ የያዘው አባዜ ያንቀዠቀዠውን ስም አጥፊ የስም ሌባ ውሸታም መልኩና ይዘቱ ምን እንደሚመስል በጥቂቱም ቢሆን ሳልዳስሰው አላልፍም ፡፡

በመሠረቱ ወደ አሜሪካ የሚመጡት ወገኖቻቺን ወጣቶቹ ልዩ ልዩ ትምህርት ለመቅሰምና

ቁምነገር ያዘለ እውቀት ገብይቶ ለመመለስ ሲሆን ሽማግሌዎቹም ቢሆኑ የቅዠታም ቄስ ነኝ ባይ ተላላኪነት ፈልገው ሳይሆን ለሕክምናና ልጆቻቸውን አምጥተው ለማስተማር እንጂ ሕዝብን ከሚከፋፍልና ደሆች ቤተክርስቲያኖችን ከሚዘጋ መናፍቅ ተሐድሶ ቄስ ነኝ ባይ ጋር ዲያብሎስ የተጠናወታቸው ጀሌዎቹ ካልሆኑ በስተቀር አብሮ ለማገልገል የሚጠይቅ ወይም ቄስ ተብዬው ካሉበት የሚመጣ ያለመኖሩ የሚያረጋግጠው የፈሳች ዝንጀሮ መስለው ለብቻቸው እንደ ቁራ የሚጮሁ ምቀኛና ካሁን ቀደም እንደተዋረዱት ሌላ አዋቂ ቄስ ከመጣባቸው እንደሚዋረዱ ሥራቸውና ችሎታቸው ስለሚመሰክርባቸው ይህን በመሰለ ሁኔታ እያወናበዱ እድሜአቸውን በጉራና ስም በማጥፋት እንደሚገፉ ሥራቸው በቂ ምስክር ነው ፡፡ እኒህም ሕዝብን ሊያፋጁ ሲሉ በእኩይ ተግባራቸው በሊቀ ጳጳስ ከሥልጣናቸው የተወገዱት ቄስ ተብዬ ከነ ግልገሎቻቸው ናቸው ፡፡

በጣም የሚገርመው ዓይን ያወጣው ቅጥፈታቸው ያጋባ ይመስል አግብቶ የፈታና ያገባ በማለት ጥያቄ መጠየቃቸው አስገርሞኟል ‘’ዐይን የራሱን አያይ’’ የሚባለው እውነት ነው ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እንዲህ ያለ ውሸታም መናፍቅ በየቤተክርስቲያኑ ሴቶችን እያፈራረቀ የሚያሳድር በየሔደበት ሕዝብን ከሁለት የከፋፈለ በሊቀ ጳጳስ ታግዶ እግዱን በሥልጣኑ ሽሮ ያገለገለ ወዘተ.......እነዲህ ያለው ዲያቆንን ማገድና መከልከል አይችልም የማገዱ ሥልጣን የኤጲስ ቆጶሱ እንጂ የእንዲህ ዓይነቱ ቤተ ክርስቲያንን ያረከሰ ቄስ ነኝ ባይ አይደለም ፡፡

ጥያቄ አቅራቢው የኔን ስም ሰርቀው ከእውነቱ ተከስተ በማለት በስሜ በመጻፋቸው በውሸታምነታቸው ስለተጋለጡ እንደዚህ ዓይነቱ የመቀባጠር ጽሁፍ በማንም ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የማይገባ መሆኑን አሳስባለሁ ፡፡

እውነቱ ተከስተ የሚለው የኔ ስም ለመሆኑ ‘’ጥቅሙ ምን ይሆን’’ ‘’ዓይን ያወጣ ቅጥፈት’’ ‘’የማያባራ ቅዠት’’’’ነግ በኔ’’ የሚሉት ጽሁፎች በትክክል ያርጋግጣሉ ፡፡

ቅጥፈት ሲበዛ ለቅስፈት ይዳርጋል

ነሐሴ ቀን ሺህ .