Thursday, June 21, 2012

Behaset Yetedafene Ewnet Sikeset

ሚያዝያ ፫ ቀን ፪ሺህ ፪ ዓ፣ም




በሐሰት የተዳፈነ እውነት፣ ሲከሰት፣

ይህ በኣቡጊዳ ድኀረ ገጽ ኦቶ ዺቦጆ የከተበውን የማያወላውል እውነት የሚደግፍ ጽሁፍ ነው ፡፡

ስለ ካንሳስ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ቄስ አስተርአየ ጽጌና ደንገጡሮቻቸው ፀረ ማርያምና ፀረ ምእመናን የነበረው ዉንብድናቸው ከሐቀኛው የብዕር ሰው ከዲቦጆ እ፣ኤ፣አ፣ በ፭ ፣፫፣፲፪ በአቡጊዳ ድኅረ ገጽ ላይ በአጭር ተከትቦ ሳየው በጣሙን ተገረምኩ አንባብያንም አድንቀውታል

ሁኔታውን እንደገመገምኩት ቀደም ሲል እውነቱ ተከስተ የተባለው የብዕር ሰው የቄሱንና የግብረአበሮቻቸውን አጸያፊ ድርጊት በማውገዝና በመቃወም ፣

፩ኛ ጥቅሙ ምን ይሆን?

፪ኛ ዐይን ያወጣ ቅጥፈት፣

፫ኛ የማያባራ ቅዠት፣

፬ኛ በዛና ጠነዛ፣ በሚለው የጽሁፍ አርእስት እውነቱን አፍረጥርጦ በመግለጽ በጎላ መስታውት ቢያሳያቸውም ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ከድርጊታቸው ሊታቀቡ አልቻሉም፡፡

የካንሳስ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ምእመናን አሳጧት እንጂ ቅልብጭ ያለች ጥሩ ቤተ ክርስቲያን ነች ሐቀኛ ቄስ ስለሌለባት ባዶዋን ቀርታለች፡፡

በዚህ ቤተ ክርስቲያን የሚያገለ̎ግሉት ቄስ አስተርአየ ጽጌ የተባሉት ያለፈው የሕይወት ታሪካቸው በግልጽ ሲተነተን ከደብረሊባኖስ እንደወጡ በአዲስ አበባ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ በምቀኝነት ተነሳስተው የሥላሴን ዲያቆናት ድንገት በዱላ ቀጥቅጠውና በአስፋልት ላይ ዘርረው (ይሙቱ ይዳኑ አይታወቅም) ጥለዋቸው ወደ ኬንያ ኮብልለው ለመጥፋታቸው ራሳቸው እንደ ጉራ ሲያወሱት የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ቅስና አልተቀበሉም አልቀደሱምም ይህንንም እራሳቸው በይፋ ገልጸውታል ስለዚህ ቅዳሴ የመቀደስ ችሎታ የላቸውም ፡፡

ከኬንያ ወደ አሜሪካ እንደመጡ ዲሲ ገብተው ካህናቱን በአሉባልታ ሐሰት እያተራመሱ ሲነቁባቸው ወደ ሲያትል ኮበለሉ ፡፡ ከሲያትል ሕዝቡን ከሁለት ከፍለው ስላፋጁ ተባረው ወደ ሴንትሉስ ፈረጠጡ ፡፡ ሴንትሉስ የማርያምን ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከሁለት ከፍለው ወደ አልታወቁበት ወደ ካንሳስ ተጓዙ ፡፡ የካንሳስ ኪዳነምሕረትን ምእመናን አፋጅተው ሊያደባድቡ ሲሉ እራሳቸው የመረጧቸው ሊቀጳጳስ መጥተው ጉዳዩን አጣርተው ምእመናኑን ሲጠይቁ ‘’ይህ ቄስ አይደለም ከዚህ ይወገድልን ‘’ በማለት ለቄሱ ውጣ ! ! ! እያሉ ሲጮሁባቸው በመመልከታቸው የአመራርና የአገልግሎት ችሎታ የሌላቸው እመቤታችንን ኃጢአተኛ ነች የሚሉ ፀረ ማርያም በመሆናቸው ባላቸው ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው አግደዋቸው ሔደዋል፡፡ሕዝቡም ጭቅጭቅና ፀብ ስለሰለቸው ከሁለት ተከፍሏል ፡፡

የቀድሞው የአመራር ኮሚቴ ሰብሳቢና ሌሎችም መድኃኔ ዓለም በሚል ስያሜ ቤተ ክርስቲያን መስርተው የቄሱ የቅርብ ደጋፊ የሆኑት አድር ባዮች ለምእመናኑ ሳያሳውቁ ሴንትሉስ ድረስ በመሔድ ጠርተው አመጧቸው ለምን ቢባል ለምስጢራዊ ጥቅማቸው ሲሉ ነው፡፡

ከመጡም በሗላ የመድኃኔ ዓለምን ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከሁለት ከፍለው ሲያፋጁአቸው ከሦስቱ የጥቅም አበሮቻቸው በስተቀር አብዛኛዎቹ ይህ በጳጳስ የታገደና የተወገዘ ቄስ ስለሆነ በእርሱ አንገለገልም ብለው ጥለዋቸው ስለሔዱ በሦስቱ ጋሻጋግሬዎቻቸው ተመክተው የሊቀጳጳሱን ሥሌጣን ሽረው የሚያገለግሉ ስለሆነ የሲኖዶስ ተቃራኒ ከፍተኛ ወንጄለኛ ናቸው፡፡

የተማሩ ካህናት ሲመጡ በሐሰት ስማቸውን እያጠፉና እየወነጀሉ በደጋፊዎቻቸው ተባባሪነት ያበሯቸዋል ፡፡ እኒህ ቀጣፊ ቄስ ትልቁ ማወናበጃቸው የተከበሩትን የሐዋርያት ምትክ የቤተ ክርስቲያን አባቶች የሆኑትን ብፁአን ጳጳሳትና ካሕናትን ጭምር ተመቸኝ ብለው ጎሳ እየጠቀሱ ስም በማጥፋት የሚሳደቡና እርሳቸው ከሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን አባት ጳጳስ እንዳይመደብ በማድረግ በሥጋው ደሙና በሌሎችም የሚያጭበረብሩት ወንጀላቸውና የሥራ ድክመታቸው ይፋ እንዳይወጣባቸው የሚያምታቱ ለመሆናቸው በግልጽ ታውቆባቸዋል ፡፡

እኒህ ቄስ የሐሰት ከረጢት በመሆናቸው ምንም የማያውቁትን በኦርቶዳክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር በትምሕርት ተኮትኩተው ያላደጉትን አላዋቂ አወናባጅ ኮሚቴዎችን የሙጥኝ ብለው ሐሰቱን እውነት እያስመሰሉ በመስበክ እድሜአቸውን የሚያራዝሙ በበጎች መካከል የገቡ ተኩላ ናቸው

ከዚህም በተጨማሪ መንፈሳዊውን ሕይወት የማይከተሉና በቂም በቀል ተነሳስተው ሰውን ለመጉዳት የሚሯሯጡ ከመሆናቸውም በላይ ይህን ስህተታቸውን ለመሸፈን ሐሰቱን እውነት በማስመሰል ለምእመናኑ ትምህርት ሲሰጡ “ቂም በቀል ኃጢአት አይደለም እኔ ቂም አልፍቅም ቂም የማትይዝ አህያ ብቻ ነች “ ብለው ያስተማሩ ቀንደኛ አጭበርባሪ ናቸው ፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ስለአገዷቸው እርሳቸውን በመዝለፍ የሐዋርያትን ሥልጣን አቃለው ማን አለብኝ በማለት ከታገዱበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ከሕግ ውጭ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አድራጎታቸው ተወግዘው መባረር የሚገባቸው ናቸው፡፡ እሳቸው ግን ምን ሰው አለና ብለዋል ፡፡

እንዲያው ለመሆኑ እኒህ ሰው መረን እንደተለቀቀ አለሌ ኮርማ ሆነው ግዝቱን የሚያፈርሱበትና ከሕግ ውጭ የሚፏልሉበት በሥጋው ደሙና በቅዳሴው ሥር̎አት የሚያታልሉበት ምክንያት የቅስናውን ሥልጣን በገዛ ራሳቸው የሾሙ ከሐዋርያዊ ጳጳስ ያልተቀቡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት ያልቀደሱ ከቅስናው ሥርዓት ጋር የማይተዋወቁ በጳጳስ ባለመቀባታቸው ሐሰት የሚያናግርና የሚያንቀዠቅዣቸው የተጠናወታቸው ዲያብሎስ በመሆኑ አይደለምን ? ነው ፡፡

ወደ ሥልጣናቸው ከመመለሳቸው በፊት ሊጠየቁ የሚገባቸው ፡

ሀ. የቅስናውን ሥልጣን ሥርዓቱን አከናውነው ቅስና የሰጧቸው ጳጳስ ማን ናቸው ?

ለ. የቅስናው ሥርዓት የተካሔረው የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው ?

ሐ. በእለቱ ሥርዓተ ቅዳሴውን ያከናወኑት ካህናትና ዲያቆናት እነማን ናቸው ?

መ. የድቁናና የቅስና ማዕርገ ክህነት ለመቀበላቸው የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ ግዴታቸው ነው፡

ሠ. ኢትዮጵያ የቀደሱባቸው ቤተ ክርስቲያኖች ስም መግለጽ አለባቸው ?

ረ. ከገዳሙ ትምሕርት አቋርጠው እንደወጡ ስብከተ ወንጌል እንዲለማመዱ የተላኩበትን ደብዳቤ ቋሚ ሠራተኛ ቄስ ሆነው እንዳስተማሩ አስመስለው ስለሚያታልሉ ማስረጃው መጣራት አለበት ፡፡

ይህ ካልሆነ ግን የቅስና ሥልጣቸው ከሚፈጽሙት ተግባራቸውና ከሚያስተምሩት ትምህርት ጋር ሲገናዘብ ውሸትና ቅጥፈት የተሞላበት አጠራጣሪ ነውና የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት እንዳያፋልሱ ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ ቄሱን አግዶና አውግዞ በተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳያገለግሉ በማባረር በኢንተርኔት ለሕዝብ መገለጽ አለበት ፡፡ ያለበለዚያ ግን የእሳቸው መሰል ጮሌዎች ባልተሰጣቸው ሥልጣን ከማይታወቁበት ሥፍራ በመሔድ ቄስ ነን ፡ መነኩሴ ነን፡ እያሉ በማወናበድ ምእመናኑን ስለሚያስቱና ስለሚዘርፉ በጥብቅ እርምጃ መወሰድ ይገባዋል እላለሁ ፡፡

እስከዚያው ምን መደረግ አለበት ለሚለው ፡

፩ኛ. ሊቀ ጳጳሱ ትክክልም ይሁኑ አይሁኑ ተጠርተው መጥተው በተሰጣቸው ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ካገዷቸው እግዱን አክብረው ለሚመለከታቸው የበላይ አካላት አመልክተው ሳያሽሩ ማገልገል በፍጹም አይችሉም የተሰጣቸው ሥልጣን በጳጳስ ተወስዷል ፡፡

፪ኛ. በሊቀ ጳጳስ የታገደ ቄስ መቀደስ ፣ ማቁረብ ማሳለምና ማጥመቅ አይችሉም ፣ እሳቸው ግን በንቀት ስለሚያገለግሉ ሁሉም በበኩሉ እንዲያወግዛቸው፡፡

፫ኛ. የሊቀ ጳጳሱን እግድ የሚያሻሽልና የሚሽር ተመሳሳይ ሊቀጳጳስ ወይም የካህናት ስብስብ ሳይሆን የሲኖዶስ ጉባኤና ያገደው ጳጳስ ብቻ ነው ፡፡ ቄሱ ግን የሲኖዶስ ጉባኤና የበላይን አካል የማያውቁ ሕገወጥ ስለሆኑ መባረር አለባቸው ፡፡

፬ኛ. ምእመናኑም በበኩላቸው በታገደ ሕገጥ ቄስ መገልገል አይገባቸውም የሐዋርያትን ሥልጣን ሽረዋል ማለትነው ከባድ ኃጢአት ስለሆነ ንስሐ ይግቡ እላለሁ ፡፡

፭ኛ. እኒህ ቄስ ራሳቸው አባል የሆኑበት የካህናት ስብስብ እንዲሁም እግዱን አንተውልኛል ያሉዋቸው ሊቀጳጳስ አቡነ ይስሐቅ እግዱን የመሻር ሥልጣን የላቸውም በሥልጣን ተመሳሳይ ናቸውና ተቀባይነት የለውም የማወናበጃ ሥልት ነው ፡፡

፮ኛ. ምእመናኑም ሆኑ ኮሚቴዎቹ ስለሕጉ የሚያውቁት ነገር ያለመኖሩን ቄሱ ስለሚያውቁ እግዱ ተነስቶልኛል በማለት እያወናበዱ ምእመናኑን ከስህተት ውስጥ ጥለዋል ፡፡ ሕጉን ያወቁት አባላት ግን አስቀድመው በወቅቱ ጥለዋቸው ሔደዋል እውነተኛ የኦርቶዶክስ አማኞች ስለሆኑ የእነሱን ፈለግ መከተል ይገባናል ፡፡

፯ኛ. የሚፈጽሙት ስህተት እንዳይታወቅባቸው እውነተኛ የተማረ ሊቅ በመምሰል የባጥ የቆጡን ውሸት እየጻፉ በማምታታትና በመሳደብ በኢንተርኔት ሲያወጡ ይታያሉ የሚገስጻችው ስላጡ ነውና ምእመናን ሁላችሁ ዐይንሕ ለአፈር ብላችሁ አውግዟቸው፡፡

፰ኛ. የካሕናቱ ስብስብም ሆኑ አቡነ ይስሐቅ እግዱን አንስተናል ማገልገል ይችላሉ ያሉበት ማስረጃ የለም ውሸት ስለሆነ እግዱ እንደጸና ነው ፡፡

፱ኛ. ቄስ አስተርአየ ውርደት ልማዳቸው ነውና ከመዋረዳቸው በፊት ከሕግ ውጭ ማገልገሉን አቋርጠው በቅድሚያ ሥልጣናቸውን እንዲያስመልሱ በዚህ ጽሁፍ እናስጠነቅቃቸዋለን ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምእመናን ሆይ እኒህ ቄስ እናንተን አላዋቂ ዶንቆሮ በማድረግ ከባዱን የሐዋርያትን ሥልጣነ ክህነት አቃለው ከስህተት ውስጥ የጨመሯችሁ መሆኑን ተረድታችሁ በእርሳቸው ሥር መገልገል እንድታቋርጡና መስቀላቸውንም እንዳትሳለሙ በእርሳቸውም እጅ ቁርባን እንዳትቀበሉ ሕፃናትንም በእርሳቸው እጅ ክርስትና እንዳታስጠምቁ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕግ ሲናዶሱ ስለሚያግዳችሁ ካሁን ቀደም እውነቱ ተከስተ የተባለው የብዕር ሰው በኢንተርኔት ያወጣቸውን በአርእስቱ የጠቀስኳቸውን ሥነ ጽሁፎች ከኢንተርኔት አውጥታችሁ ብታነቡት የእኒህን ቄስ ታሪክ አበጥሮ ያስረዳችኋል እላለሁ ፡፡

የእምነታችንን ሥርዓት በጋራ እንድናስከብር ግዴታችን ነው ፡፡



አጭር ሰምና ወርቅ ቅኔ ፣

የሰውዬው ዜና ኡ ! ! ! ኡ ! ! ! የሚያሰኝ ነው ፣

ማን ይጮህልናል እኛው እናቧርቀው ፣

ይሉኝታ አጠቃን ደቋቁሶ ለቀቀን ፣

አፈሩ ቅጠሉ ዛፉ ያስተማረን ፣

ከአገርም ብንወጣ ፍጹም አለቅ አለን ፣

እኛ የለመድነው የመጽሐፉን ቃል መጠጣት ነበረ ፣

አንቆርቋሪው ሰይጣን ሆኖ የሰከረ ፣

ሰላም የሚነሳን አእምሮው የዞረ ፣

መጣና አሳየ ሕዝቡን በጠበጠው ፣

በትምሕርቱ ምትክ ክርፋቱን አደለው ፣

ቤተ መቅደስ ገብቶ ቁራ ጮኸበት ፣

ሳሎኑም ቤዝሜንቱም ጥራጊ ጣለበት ትፋቱን ተፋበት ፡፡

አብራራው አይምሬ ነኝ ፡፡