ግንቦት ፲፯ ቀን ፪ ሺህ ፪ ዓ.ም
የማያባራ ቅዠት ፡፡
ከእውነቱ ተከስተ
ሚያዝያ ፲፱ ቀን ፪ ሺህ ፪ ዓ.ም ከቄስ ተብዬ ኣስተርአየ የተጻፈውን የሚጠቅስና ያለፈውን ጽሁፌን የሚያስታውስ
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሠረተ ቢስ ከሆነው ቅዠት ያድነንና አንድ አንድ ለቅዠት ያደላቸው ቄስ ነኝ ባዮች ቅዱስ ቃል እንዲፈልቅበት ጌታ የፈጠረላቸውን አንደበት የቅዠት ስልቻ አድርገውት ሌትና ቀን ሳያርፉ እየቃዡ በየጊዜው ሰይጣናዊ ቃላት ሲጭሩና ሌሎችንም ኃጢአተኞች እያደረጉ በመኮነን እንደ ተስቦ ሕዝብን ሲበክሉ ይታያሉ ፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፵፩ እና ፵፪ ላይ እጠቅሰዋለሁ ‘’በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለምን ታያለህ? በዐይንህ ውስጥ ያለውን ምሰሶ አታይምን ? ወንድምህንም ወንድሜ ሆይ ታገስ በዐይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ልትለው እንደምን ትችላለህ ? አንተ ግን በዐይንህ ያለውን ምሰሶ አታይም? አንተ ግብዝ አስቀድሞ ከዐይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚህ በኋላ በባልንጀራህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ ሲል አስጠንቅቆናል ፡፡
ነገር ግን ቄስነኝ ባዩ አስተርአየ ጽጌ ለሕዝብ ቅዱስ ቃል ማቅረብ ሲገባቸው የሕዝብን ምክር ባለመቀበል ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው በቅዠት ባሕር እየዋኙና ፍካሬ ያሉትን የክርስቶስን ማስጠንቀቂያ ውድቅ እያደረጉ ሲሳደቡ ይታያሉ ፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፰ ከቁጥር ፩ ጀምሮ ያለውን ብንመለከተው ጻፎችና ፈሪሳውያን በዝሙት የተያዘች ሴት ወደ ጌታ ኢየሱስ አምጥተው ይህች ሴት ስታመነዝር አግኝተን ያዝናት የሙሴ ሕግ በድንጋይ እንድትደበደብ ያዛል እንግዲህ አንተ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ ? አሉት እርሱም መልሶ ከናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ ድንጋይ ይጣልባት አላቸው እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ የሠሩት ከርሷ የበለጠ ከባድ ኃጢአት ተገልጾባቸው ሁሉም አንድ አንድ እያሉ ወጡ ጌታችን ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም ቆማ ነበረና ወደ እርሷ ተመልክቶ አንቺ ሴት የሚከሱሽ ወዴት አሉ? በማለት ሲጠይቃት የማየው የለም አለችው ጌታ ኢየሱስም እኔም አልፈርድብሽም ወደ ቤትሽ ሒጂ ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ ኃጢአት አትስሪ ብሎ አንጽቶ ሰደዳት፡፡
ወገን እባካችሁ ቄስ ተብዬው አስተርአየ ምን ዓይነት የበቁ ሆነው ነው በየጊዜው በውሸት የሰውን ኃጢአት በመዘርዘር ስም እያጠፉ የሚቃዡት ? እኩይ ተግባራቸውና አስነዋሪው ኃጢአታቸው በሙሉ ቢዘረዘር ከአሁኑ የባሰ ለሰው እንዳይታዩ ከቤዝመንቱ በታች እንደ ቀበሮ ጉድጓድ ምሰው ከነ ጀሌዎቻቸው በተደበቁ ነበር ፡፡ ሆኖም ቢፈልጉ ከማጀት ይግቡ እንጂ የአንባቢያንን ጊዜ ላለመሻማት ጥቂቶቹን ጠቀስ አደርጋቸዋለሁ ፡፡
’’የቀበሮ ባሕታዊ ከበጎች መካከል ገብቶ ይሰግዳል’’ ይባላል እንዲያው ለመሆኑ ቀንደኛ ከፋፋይ ከርስዎ የበለጠ ማን ሆኖ ነው ሌሎችን የሚኮንኑት ? ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው ይባላልና ቢመከሩ አሻፈረኝ ብለው አስነዋሪ ተግባራትን በስውርና በይፋ ሲፈጽሙ ዘመናት አሳልፈው መጋለጫዎ ስለተቃረበ ጉድዎ በይፋ እስኪገለጽብዎ ለማያውቁዎት በሚጭሩት ጽሁፍ እያወናበዱ ይቃዣሉ ፡፡
ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስን ከነብሰ ገዳዩ ካድሬ ከመላኩ ተፈራ ጋር ሆነው ወንጄል ፈጽመው ነው የመጡት ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ፈርመው ለቀው ጠፍተው በኬንያ በኩል አሜሪካ ገቡ እዚያው መሞት ነበረባቸው በማለት ያላዩትን ሀሰት በለመደው አፍዎ ሲወሸክቱና ጎሳ እየለዩ ሕዝብን በሚከፋፍሉበት የከረፋ ልሳንዎ ጎንደሬ ጳጳሳት ተሰባስበው እያሉ ሲኮንኗቸውና በወሬ ስማቸውን ሲያጠፉ የነበረውን ለመሸፈን ሲያወናብዱ ሰው ምንይለኛል የማይሉ ዓይነ ደረቅ ቀጣፊ ነዎት ፡፡ ብፁእ አቡነ መርቆሬዎስ ከእርስዎ የበለጡ የተማሩ ስለሆኑ ቅጥፈትዎን ይረዳሉና አያታሉ ፡
ብፁእ አቡነ ጳውሎስንም ሊቃውንቶች አልቀዋልና ሰው የለኝም ናልኝ ብለው ደወሉልኝ እያሉ ሲወሸክቱና ለቅጥፈት ደጋፊነት ባሰለጠኗቸው ጀሌዎችዎ አማካይነት ሲያስወሩና መጽሐፋቸውን በመጥቀስ ሲያመሰግኗቸው የነበረውን ረስተው በዚህ ጽሁፍዎ ሲሳደቡ ለህሊናዎ ምንም ስለማይሰማዎ ለስድብ የሚሰማራው ዲያብሎስ ተጠናውቶዎታል ማለት ነው ፡፡ ብፁእ አቡነ ማትያስንም ቀድሞ ስማቸውን ጠርተው የማያውቁትን እራስዎ እንዲመጡ ፈቅደው ካንሳስ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ከመጡ በኋላ ለሚጠይቁዎት ተገቢ መልስ መስጠት ሲገባዎት ሕዝቡን ከሁለት ከፍለውት አብዛኛው ሕዝብ ይሄ ቄስ አይደለም ወንበዴ ነው ይወገድ እያለ በመጮህ ሊያደባድቡት በመድረስዎ ብፁእ አቡነ ማትያስ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ስለሚያስገድዳቸው እርስዎን በእኩይ ተግባርዎና በመናፍቃዊ ትምህርትዎ ሕዝበ ክርስቲያኑን የከፋፈሉትን ቄስ ማገድ ግዴታ ሆኖባቸው ከሥልጣንዎ አግደው ሕዝቡን ከድብድብ በማዳናቸው መመስገን የሚገባቸው እንጂ እንደርስዎ ባለው የረከሰ አንደበት ባልተሰደቡም ነበር፡
መሰርይነትዎን ለመሸፈን በውጭ አገር የተበተነውንና እረኛ ያጣውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆነውን ሕዝብ የተቀደሰ ትምህርት በመስጠት በእንደርስዎ ባለው ነጣቂ ከፋፋይ ተኩላ እንዳይነጠቁ ለማዳን የተሰማሩትን የሐዋርያት ምትክ ብፁአን ጳጳሳት መነኮሳትና ካህናትን እንዲሁም ቅን አገልጋይ ዲያቆናትን የሚኮንኑና ያለ እርስዎ ጨዋና የተማረ አዋቂ ሊቅ እንዳልተፈጠረ አድርገው በለመዱት የከፋፍለህ ምራው እኩይ ተግባርዎ የሚጭሩትና የሚሳደቡት ከርስዎ የበለጠ አስነዋሪ ልክፍተኛ ያለመኖሩን በግልጽ ያሳያል ፡፡
’’አላዋቂን ለማወቅ ብትፈልግ ያለ እኔ አዋቂ የለም ሲል ታገኘዋለህ’’ይላል እርስዎም ከሊቃውንቱና ከአዋቂዎች እየተደበቁ በየ ቤተ ክርስቲያኑ ቤዝመንት ልዩ ልዩ ፍላጎቶን እያረኩ በትምህርታቸው በቅተው የተመረቁትን ብፁአን ጳጳሳት መነኮሳትና ካህናትን በሐሰተኛው ጽሁፍዎ ሲኮንኑ ይታያሉ ፡፡
’’ላላወቀብሽ ታጠኝ’’ ነውና በጎሳ መከፋፈሉና ማወናበዱ ያላዋጣዎት ስለሆነ በተደጋጋሚ የሚረጩት የሰውን ልቦና መስለቢያ ጽሁፍዎን ማንኛውም ሰው ያወቀብዎት በመሆኑ ከዚህ የባሰውን ውርደት ከመከናነብዎ በፊት ከቅጥፈት ጽሁፍዎና ከእኩይ ተገባርዎ እንዲታቀቡ አጥብቄ አስጠነቅቆታለሁ ፡፡
አንድን ነገር መቶ ጊዜ ቢደጋግሙት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም በዚሁ ጽሁፍዎ ላይ የኪዳነ ምሕረትን ሕዝበ ክርስቲያን ካቶሊክ እያሉ ልቅ የሆነውን ያልታረመ አንደበትዎን በመክፈት በፍካሬዎች ጽሁፍዎ ላይ ጠቅሰው ተሳድበዋል ለመሆኑ ‘’ጥቅሙ ምን ይሆን’’ እና ‘’ዐይን ያወጣ ቅጥፈት’’ የሚለውን ጽሁፌን አንብበውታልን ? አላነበቡትምና ‘’ጉግል’’ ከሚለው ኦብሳይት ገብተው ‘’ከእውነቱ ተከስተ’’ የሚለውን ካወጡ ያገኙታልና ያንብቡት እርምት ይሰጥዎታል ፡ ወገን እባካችሁ ሌሎቻችሁም ለአንድ ጊዜ ተቸግራችሁ አውጥታችሁ አንቡት ድጋሚ ዝርዝር ውስጥ አልገባም ፡፡
እባክዎን ቄስ ተብዬው በካንሳስ ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን መጀመሪያ ከሳሙኤል ጋር የፈጠራችሁት ጸብ እሱ ላስተምር ሲል እርስዎ በምቀኝነት መንፈስ ተነሳስተው አያስተምርም ብለው በመከልከልዎ ፀቡ ተባብሶ እርስዎ ወደ ፈጠሩትና እመቤታችን ኃጢአት አለባት ብለው በማስተማርዎ የተነሳ የሕዝብ ክፍፍል እንደመጣ በሳሙኤል ምክንያት የጻፉት ጽሁፍ ምስክር ነው ፡፡
የኪዳነ ምሕረት ምእመናን የእርስዎ ትምህርት አይገባንም በአውደ ምሕረቱ ላይ ሁልጊዜ የሚያቀርቡት ስድብ ነው መስማት አንፈልግም ሳሙኤልና ሌሎቹም ከእርስዎ ጋር እንደቀድሞ በተራ አስተምሩ ከማለታቸውም በላይ የአመራር ኮሚቴው ደብዳቤ ቢጽፍልዎትም በምቀኝነት የተጠናወተዎት ዲያብሎስ ስላልፈቀደልዎት አሻፈረኝ በማለትዎ ሰላም የነሱት ሕዝብ ውጣ !! ቄስ አይደለህም ብሎ አባረሩዎት እንጂ ሕዝቡ አባቶቻቸው የሞቱላትን ተዋሕዶ እምነቱን ትቶ ካቶሊክ አልሆነም ፡ ለዚህም ከጽሁፎቼ አጥጋቢ ምላሽ አግኝተዋል ካቶሊክና ልዩ ልዩ የመናፍቃንን ትምህርት የሚያስተምሩ የእመቤታችንን ስም ከመጽሐፉ የሰረዙ ቀንደኛ መናፍቅ እርስዎ ለመሆንዎ ሕዝቡ የሚያውቅ ከመሆኑም በላይ በቂ ማስረጃ ሊቀርብብዎት የሚችል ነው ፡፡ ስለዚህ ‘’ወሀ ቢወቅጡት እምቦጭ’’ ነውና ምን እንደሚፈልጉ አይታወቅም ቀንደኛ ጠላትዋ ስለሆኑ እንደ ደህና ሰው የእመቤታችንን ስም ደግመው እንዳያነሱና ሕዝቡን ያለ ሥራው እንዳይኮንኑ እስጠነቅቆታለሁ ፡፡
መስከረም ፲ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓ.ም በጫሩት ጽሁፍዎ ላይ ‘’አጫብር በሚለው ዜማ ዓይነት ጾመ ድጓ፡ መስተጋቡን፡ ክስተቱን፡ አርያሙን፡ ጮኬአለሁ እነሱም ቢሆኑ አቅጣጫዬን ስቀይር በነበሩበት የሉም’’ ብለዋል ሰይጣናዊው ተግባርዎ አሸንፎ ወሰዳችው ማለት ነውን ወይስ የለመዱትን ሐሰት ይቀላምዳሉ ? ለመሆኑ እድሜ ልክዎን ቄስነኝ ብለው በቅስና ሥራ እያጭበረበሩ መኖርዎ ይታወቃል ለምን የተማሩ ሊቃውንት ያሉበትን እየተው እንደ ፈሳች ዝንጀሮ ለብቻዎ ተለይተውና አንዲት ቤተ ክርስቲያን ለብቻዎ ታቅፈው ችሎታዎ በማይመዘንበት ቦታ እየተደበቁ ይቀመጣሉ ? የሆነስ ሆነና ቢጠቅሱት በአንዱም ትምህርት ስላልተመረቁ ‘’ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል’’ እንደሚባለው ይቅር ባዩ አምላክ አዞልዎ ከቅዳሴውና ከኪዳኑ አቅም እንኳ ችሎታ ሳይኖርዎ አሜሪካ መጥተው በጉራ ብቻ እየተውረገረጉ ታክሲ ነጂ በመሆን ሳንቲም እየለቀሙ ዕድሜዎን ገፉት ፡፡ በቃረሙት ትምህርት ምትክ ተንኮልና ምቀኝነት መከፋፈልና ሴሰኝነትን ተክተውበት በዚያውም ላይ የሰውን ሰላም እየነሱ ዘመናትን ቆጠሩ ፡ ቀደም ባለው ጽሁፍዎ ላይ ዐይነ ስውር አባቶችን እመራ ነበር ብለው ተመጻደቁ እንጂ በአንድም ትምህርት መመረቅዎን አልገለጹም አልተመረቁምም፡፡
ችሎታ የሌሎት ደካማ ጉረኛ መሆንዎን በግልጽ ያስመሰከሩት አቶ ሰሎሞን ረታ በተባሉት ሰው የሠርግ መልስ ላይ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ምግብ ሊባርኩ ተነስተው በትምህርት ችሎታቸው ተመርቀው የተመሰከረላቸውን መሪጌታ ነቢዩ የተባሉትን ቄስ ወደ እርስዎ ና ብለው ጠርተው አጠገብዎ ካቆሟቸው በኋላ የመነጋገሪያውን ‘’እስፒከር’’ ድምፅ ማጉያ ይዘው እሱ እያለ እኔ መናገር አይገባኝም ነበር ሊቅ ነው ብለው ሳያስቡት በትምህርት ደካማነትዎንና ሊቃውንቶች የሉም ሁሉም ዶንቆሮ ብቻ ነው የተሰበሰበው እያሉ ሲወሸክቱ የነበረውን ረስተውት ሳያስቡት የራስዎን አላዋቂነት አጋለጡ ፡፡
ሆኖም ከተማሩት ጋር አብሮ ማገልገል ስለማይሆንልዎና ጠፋ ያሉትም እውቀት ስለሌለ በቅናት የተመረዘው ልቦናዎ ባፈለቀው ምክንያት የመሪጌታውን ስም አጥፍተው እንዲባረሩ አደረጉ ፡ የሴንቱሉሱ ጓደኛዬ ስለ እኒህ ቄስ ነኝ ባይ ሲነግረኝ ‘’እኔ ቄስነቱ ባይዘኝ ኖሮ በጣም እርኩስ ነበርኩ’’ ብለዋል ሲል ያጫወተኝ ትዝ ሲለኝ እውነትም ከዚህ የበለጠ እርኩስነት ምን ሊያመጡ ነው ? ያልፈጸሙት እርኩስነት የለም ወደፊት የሚጭሩትን ስድብና ተንኮል ካላቆሙ የተቀሩት ለሰው ጆሮ የሚያስጠሉት አስነዋሪ አፈጻጸሞቻቸውን በዝርዝር ለማቅረብ እገደዳለሁ ፡፡
መቼም ነገርን ነገር ያነሳዋልና ባለፈው ጭረው በጀሌዎ በአቶ ይበቃል ያረጋል በኩል ባስተላለፉት ጽሁፍ ሁለት የሲኖዶስ ሊቃውንት የማርያምን ጉዳይ በተመለከተ ቀሲስ አስተርአየ መጥቶ ያመልክት ብለዋል ያሉትን እየደበቁ የሲኖዶሱን ሊቃውንት ይኮንናሉ ስለ አስተዳደርና ስለ ጉባኤ ሕግ ባለማወቅዎ እንጂ ለመሆኑ ተበደልኩ ፍርድ ተጓደለብኝ የሚለው የታገደው ወገን እቤቱ ወይም እንደርስዎ እቤተ ክርስቲያን ቤዝሜንት ሕንፃ ውስጥ ሆኖ እየወሸከተ ጭሮ በሚልከው ወረቀት ብቻ ዳኝነት ታይቶ ውሳኔ የሚሰጠው የት አገር ነው ? አቤቱታውን ሰሚ የሲኖዶሱ ተወካይ ዳኞች ካሉበት ሔደው በጽሁፍም ሆነ በቃል አስረድተው ማስወሰን ሲገባዎ ከመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ባለው ቤዝሜንት ከፈለጉት ጋር በሚዳሩበት ከፍል ተቀምጠው ማቅራራትና ሊቃውንቱን መስደብ ዲያብልስነት ስለሆነ ሊቃውንቱ ባዘዙዎት መሰረት ሔደው ያመልክቱ ከአሁን ወዲያ በማርያም ጉዳይ ቱልቱላዎን አይንፉ ይታገሱ ፡፡
ለመሆኑ ፍካሬ ኢየሱስ እንደርስዎ ላለው መናፍቅና ቄስ ነኝ ባይ ብፁዐን ጳጳሳትን የተከበሩ መነኮሳትንና ዐእይንተ እግዚአብሔር ካህናትን እንዲሁም ዲያቆናትን እንዲሳደቡ ይፈቅድልዎታልን ? አይፈቅድም እንደውም ስድብ እግዚአብሔር የሚጠላው ታላቅ ኃጢአት ነው ፡፡ መፈክረ ዲያብሎስ ያሉትም የእርስዎን እኩይ ተግባር አጉልቶ የሚያሳይ መነጽር ስለሆነ የተጠናወተዎትን የዲያብሎስን ፈቃድ ለመፈጸም ቆርጠው የተነሱ መሆንዎን ያመለክታል ፡፡
የርስዎ ቢጤ ተመጻዳቂ የሠሩትን ልግለጽልዎ አንዲት መነኩሲትና ዲያቆን በአል ለማክበር ወደ ሩቅ ቤተ ክርስቲያን ሲጓዙ መሸባቸውና አንዲት ባዶ ጎጆ ቤት አግኝተው ለማደር ከገቡ በኋላ በመንገድ የደከመውን ወገባቸውን ጥቂት አሳርፈው እማሆይ ሌሊት ተነስተው ጸሎት ሲያደርሱ ‘’አምላኬ ! አምላኬ ! አቤቱ ይቅር በለኝ እኔ በሌሊት ተነስቼ ቆሜ እለምንሀለሁ ዲያቆን ግን ተኝቶ ፈሱን ያንዛርጣል’’ ብለው ሲጸልዩ ዲያቆኑ ይሰማቸው ኖሮ ከምኝታው ቀና ብሎ ‘’እማሆይ እማሆይ’’ ሲላቸው አቤት ልጄ ይሉታል እሱም መልሶ እባከዎን መንግስተ ሰማያት በማታለል የሚገባበት ቤት አይደለምና አርፈው ለራስዎ ይጸልዩ አላቸው ይባላል ፡፡ ቄስ ተብዬ አስተርአየም እባክዎን ይታገሱ አይመጻደቁ ኢትዮጵያ ቢሆን ኖሮ የተከበሩትን ጳጳሳትና መነኮሳት የሚሰድቡበት ሐሰተኛው ምላስዎ በተገረዘ ነበር አሜሪካ ነውና ተመቸኝ ብለው በውንጀላ የከረፋውን ራስዎን ጨዋና ጻድቅ በማድረግ የሌላውን ስም እያጠፉ አይሳደቡ እንደርስዎ ያለው ቄስ ነኝ ባይ ወንበዴ መናፍቅ ሕዝቡን በማታለል እንዳይጫወትበት ከነብሰ በላው አውሬ እንዲጠበቅ እያስተማሩት ነውና እንደ ጀሌዎችዎ ወደ ዲያብሎሳዊ ሥርአት አይምሯቸው ይታገሱ ፡፡
በክፍል ፩ ፍካሬ ኢየሱስ ጽሁፍዎ የጠቀሱት ‘’የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ቦታ ላይ ቆሞ ስታዩ አንባቢ ያስተውል’’ የሚለው በትክክል እርስዎ በቤተ ክርስቲያኑ አውደ ምሕረት ላይ ቆመው ከአፍዎ የሚያፈልቁትን ስድብና ርኩሰት የሰማ ከማስተዋልም አልፎ ከፊቱ ባለው መቋሚያ ዠልጦ ቢያባርርባዎ ደስተኛ ነበር ፡፡
ከ ፩ እስከ ፲ ቁጥር በዘረዘሩት አስነዋሪ ጽሁፍ ውስጥ የተጠቀሱት አሁን እርስዎ የሚፈጽሟቸው እኩይ ተግባራት ናቸው ፡፡ ከእነኚህም በሁለተኛው ቁጥር ብዙዎችን ያስታሉ የሚለው እርስዎ ከማሳትም አልፈው ሕዝብን ይከፋፍላሉ ፡፡
በሰባተኛው ቁጥር ብዙዎች መሰናክል የሚለው የሰላም የፍቅር መሰናክል መሆንዎ በማንም ዘንድ የታወቀ ነው ፡፡
በስምንተኛው ቁጥር እርስ በርስ መጣላት የሚለው በየደረሱበት ሕዝቡንና ካህናቱን የሚያፋጁትና የሚያጣሉት እርስዎ ለመሆንዎ ግልጽ ነው ፡፡
በዘጠነኛው ቁጥር መካድ የሚለው የተናገሩትንና ያደረጉትን ዐይኔን ግምባር ያርገው የሚሉ ከሐዲ በመሆንዎ ከአምስት ያልበለጡ ጀሌዎች ተማሪዎችን አፍርተውበታል ፡፡
በአስረኛው ቁጥር የሐሰተኛ ብዛት የሚለው በተቀደሰው አውደ ምሕረትም ሆነ
በየደረሱበት ሐሰቱን እንደ እውነት እውነቱን እንደ ሐሰት አድርገው በማቅረብ የሚዘላብዱ የሐሰት ከረጢት ማን ሆነና ነው ይህን የጠቀሱት ? ‘’አንድ የከተማ ሰው ከባላገር ለሚመጣው ዘመዱ አንተዬ ብሳና እንጨት ይነቅዛል እንዴ ?’’ ብሎ ቢጠይቀው ለእንጨት ሁሉ ያስተማረ ማን ነው ? ብሎ መለሰለት ይባላል ፡፡ ላላወቀብሽ ታጠኝ ነውና ቄስ ተብዬው ቀንደኛ የተንኮል መምህር ኖት ፡፡
በአስራ አንደኛው ቁጥር የፍቅር መጥፋት የሚለው ማንም ሰው ይፍረደኝ ቄስ ተብዬው አስተርአየ በኖሩበት ከተማና ባገለገሉበት ቦታ ሁሉ በእሳቸው ከፋፋይነት ፍቅር ያልጠፋበትና ሰላም ያላጣ ሥፍራ የለም ፡፡
በአስራ ሁለተኛው ቁጥር ውሸታሙ ሁሉ በየቦታው ሰባኪ መሆን ሲሉ በውዲቷ አገራችንም ሆነ በውጭ ያሉት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል በሕዝቡ ጆሮ በሚያንቆረቁሩት ሰባክያን ምቀኝነትና ክፋት ተጠናወተዎት ሕዝብ መከፋፈልን እንደ ትምህርት በሚቆጥሩት በርስዎ የከረፋ አንደበት ውሸታም ተብለው መዘለፋቸው በጣም አሳዛኝ ነውና ተመልካች ይፍረደው ፡፡
በአስራ ሦስተኛው ቁጥር ርኩሰትን የሚፈጽሙ ያሉት ሴትን ከባሏ ለይቶ ከሚያድሩበት ቤተ ክርስቲያን ክፍል ዉስጥ ከማሳደር የበለጠ ርኩሰት የለምና ባላዩት ነገር እንዳዩ አድርገው በውሸት ርኩሰት የሚፈጽሙ ብለው መጻፍዎ ውሸታምና እርኩስነትዎን በይፋ ያጋልጣል ፡፡
በአስራ አራተኛው ቁጥር ላይ ከዚህ ንክኪ ርቆ ላሉት ንክኪውና ርኩሰቱ ሴሰኝነቱ ስለሆነ ይህ ጽሁፍ ከእንደርስዎ ያለው መራቅ እንደሚገባ ያስጠነቅቃል ፡፡
በክፍል ሁለት ላይ መፈክረ ማርክስ ብለው የጠቀሱት የማርክስ ፖሎቲካና ቤተ ክርስቲያን የምትመራበት የእግዚአብሔር ቃል ፈጽሞ የማይጣጣሙ እንደመሆናቸው መጠን መንፈሳውያን መሪዎች የሞራል የስነ ምግባርና የር̎ኀራኄ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን ረስተው ከሥጋውያን መሪዎች የባሱ ቀጣፊዎች አስመሳዮችና አታላዮች በዙ ላሉት በማርክስ ሒደት ውስጥ እንደርስዎ ያሉት ቀጣፊዎች ተሰግስገው የማርክስ አፈቀላጤዎች ሆነው እንጂ በጊዜአችን እንደምንመለከተው በሐገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም የተቀደሰውን የኦርቶዶክስ እምነት ያስፋፉት መንፈሳውያን አባቶች እንጂ እንደርስዎ እኩይ ተግባር የተጠናወተው ባለመሆኑ እነዚህ አባቶች ባይኖሩ እንደርስዎ ባለው መናፍቅ ከፋፋይ ሕዝቡ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ባላገኘም ነበር ፡፡
በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር መነኮሳቱ ቅዱስ ቃል እያስተማሩ ሕዝቡን ስላደራጁት ምቀኝነት አድሮቦት ከመሆኑ በስተቀር ቅዱስ ቃሉ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፰ እስከ ፴ ባለው በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ብሎ ባዘዛቸው መሰረት እንደ እርስዎ ያለውን ቀጣፊና ከፋፋይ ቄስ ነኝ ባይ በስልጣናቸው እያስወገዱ ከሕዝቡ ጫንቃ የሚያወርዱትን ከመኮነንና በከንቱ ስም ከማጥፋት ያቋረጡበት ጊዜ የለም ፡ ይህ ምንኛ መረገም መሆኑን ማንም ያውቀዋል ፡፡
የማርክስ መፈክር ባሉት ላይ ሰባኪዎችን መነኮሳትን ጳጳሳትን ቆሞ መታዘቡ የሰለቸው የሚለውና በየቤተክርስቲያኑ እየሔደ እግዚአብሔርን ገድለን ቀብረነዋል ወዘተ.... የሚል ሐተታ አትተዋል እንደርስዎ በቅዠት የሰከረው የፖለቲካው ቄስ ዲያብሎሱ ማርክስ የፈከረው መፈክር ነው ብለው ማቅረብዎ የቀንደኛው ፖለቲከኛ ቄስ ማርክስ ዲያቆን እርስዎ ለመሆንዎ የቅዠት ጽሁፍዎ በቂ ማስረጃ ነው ፡፡ ከዲያቢሎሱ ጌታዎ ጋር አብሮ ይደናቆሩ እንጂ ሕዝቡ በእንደእርስዎ ባለ ቀጣፊ ወረኛ የተቧጨረውን ሰይጣናዊ የፖለቲካ ጽሁፍ ማንበቢያ ጊዜ የለውም ፡፡
ለመሆኑ ክፍል ሦስት ብለው በጠቀሱት መፈክረ ዲያብሎስ በሚለው ላይ አቋማቸውንና ቃላቸውን እየለዋወጡ በማስመሰል የሚያታልሉትን መነኩሴዎችና ጳጳሳትን ብለው ስድብ የደረደሩት እርስዎ ማን መሆንዎ ነው ? ‘’አፍ ያለው ያግባሽ’’ አሉ አባቶች ዝም ሲባሉ ፈላብዎት የሚያረጉትን አጡ የካንሳስ ኪዳነ ምሕረትና የመድኃኔ ዓለም ምእመናን ዐይንህ ለአፈር ብለው እንደ ኩስ ጠልተዎት ከእርስዎ የተለዩትና ብቻዎን ያስቀሩዎት በማታለልዎና በማስመሰልዎ የጳጳስ እግድ በመሻርዎና እንዲሁም በሚፈጽሟቸው በተለያዩ አስነዋሪ ድርጊቶች አይደለምን ? እባክዎን አባቶችን መኮነን ያቁሙ ፡፡
ቀጥለውም የሰይጣን ሥራ የተቀደሰውን አርክሶ ማቅረብ ነው በመንበሩ ላይ የተቀመጡትን ጳጳሳት የሚቀድሱትን ካህናት ቆራቢ ነን የሚሉትን ወሯቸው ተገኘ ብለዋል ፡ የማያውቅብዎትን ያታሉ የባጥ የቆጡን እየጠቀሱ የሚቧጭሩት ጽሁፍ ምን ጊዜም ቢሆን የአሽሙርና የተንኮል ስለሆነ ሁሉም እንደ ቅዠት ይቆጥረዋል ለመሆኑ የርኩሰት ስራዎ ቢመረመርና በግንባርዎ ላይ ቢጻፍ የተቀደሰውን መንበሩንና አውደ ምህረቱን እንዲሁም ጀሌዎችዎን በኃጢአት በክለውና በዲያቢሎስ አስወርረው ያረከሱ ከእርስዎ የባሰ ቀንደኛ አውሬ አለን ? ጀሌዎችዎም ቢሆኑ ከእርስዎ የወረሱት እኩይ ተግባር ተጠናውቷቸው ያረከሱት ከመቅደሱ ውጭ ነው ፡ ኧረ እባክዎን የእርስዎን እርኩስነት ወደ ተከበሩት አባቶች አያስተላልፉ ሰሚ የሎትም ፡፡
በገጽ ሰባት ላይ ደግሞ ከላይ እንደጠቀስኩት እንደ ዲያብሎስ የብርሀን መልአክ መስለው በማታለል ሊቀርቧቸው ስለፈለጉ ቀድሞ በገዛ ፈቃዳቸው ፈርመው ሥልጣናቸውን ለቀው የፈረጠጡ ጎንደሬ ጳጳሳት ተሰባስበው እያሉ የሐሰት ወሬ ሲነዙባቸው የቆዩትን እንዲሁም በእርሳቸው ሥር ያሉትን ጳጳሳት ጭምር ከሥልጣናቸው ተወግደዋል እያሉ የባጥ የቆጡን ሲቀበጣጥሩ የነበሩትን ቅዠት ረስተውት አሁን ደግሞ ያለ አግባብ ከሥልጣን መውረዳቸውን ጠቅሰው ለመደገፍ ሞክረዋል ፡ በጊዜው ይሳደቡ የነበሩትንና የሚኮንኗቸውን የት ጣሉት ? ቅዠት ነበር ማለት ነውን ? በዚህ መልኩ ወደፊትስ ምን ያህል ይታመናሉ ? ለመሆኑ የካንሳስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሕዝብ ጣቱን የሚጠባ ሕፃን ልጅ አድርገውት ነውን ? ሕዝቡ በርስዎ እኩይና የተንኮል አፈጻጸም ከነቃብዎ ብዙ ጊዜ ሆኖታልና ብፁዕ አባታችን አቡነ መርቆሬዎስም በእኩይ ተግባርዎ ከነቁብዎ ዘመናት አልፈዋልና በቅዠትዎ ተዋረዱ ፡፡
በገጽ ስምንት ላይ በካንሳስ ኪዳነ ምሕረት ስለ ተነሳው የነገረ ሃይማኖት ጉዳይ ጠቅሰዋል ለዚህ ‘’ጥቅሙ ምን ይሆን’’ እና ‘’ዐይን ያወጣ ቅጥፈት’’ በሚለው ጽሁፌ በቂ የሆነ መልስ የሰጠሁበት ስለሆነ የአንባቢያንን ጊዜ አላባክንምና ማርያም ኃጢአተኛ ነች ካልተባለልኝ የሚሉ ከሆነ እርስዎ እንደ ፀረ ማርያሞች የፈለጉትን ይበሉ እንጂ ማንም አይልሎትም ሁለተኛ የማርያምን ጉዳይ አያንሱ የተቀረው ጉድዎ ይወጣብዎታል ብዬዎታለሁ ፡፡
በገጽ አሥራ አንድ ጽሁፍዎ ላይ ‘’እኛን ለሚመስሉ እህት አብያተ ክርስቲያናት አቀረብን’’ ያሉት በመጀመሪያ ደረጃ ከእናት ቤተክርስቲያናችሁ የሲኖዶስ አባላት የታዘዛችሁትን አልፈጸማችሁም ? ቀጥሎ ደግሞ ታላቋንና የተከበረችውን እናት አገራችን ኢትዮጵያን በለመደው ያልታረመ አንደበታችሁ ዝቅ በማድረግ የሃምሳ ዓመት የግብጽ በታች ተገዢ ጥገኛ ለማድረግ ለምን ሞከራችሁ ? ለእርስዎና ለጀሌዎችዎ ከተመቸ ውዲቷ አገራችን አፈር ትጋጥ ጥገኛ ትሁን ማለታችሁ ነውን ? ዝርዝር ሁኔታውን ‘’ዐይን ያወጣ ቅጥፈት’’ ከሚለው ጽሁፌ ተረዱ ፡፡ ሁኔታው ሲታይ ራስ ወዳዶች ስለሆናችሁ ከነ ጀሌዎችዎ ትክክለኛዎቹ ጸረ ኢትዮጵያ ናችሁ ፡
እኛን ለሚመስሉ ያሉትም ማወናበጃ አንዴ ከናት ቤተ ክርስቲያናችን የምንቀላቀልበት ጊዜ አጭር ነው እያላችሁ ስትወሸክቱ ቆያችሁና አሁን ደግሞ እኛን ለሚመስሉ እያላችሁ በማታለል መገንጠል ፈላጊዎች መሆናችሁ ድንገት ሊከሰትባችሁ ይመስላል
በገጽ አሥራ ሁለትና አሥራ አራት ላይ ስለ ጥንተ አብሶና ስለ እመቤታችን ሲጠቅሱ በስድብ እንጉርጉሮ የተሞላ ሆኖ አይቼዋለሁ ፡ ኧረ ለመሆኑ እርስዎ ሕብስቱን አክባሪና ከገንዘብ የራቁ ቅዱስ ሰው ያደረገዎ ማን ነው ? እርስዎ በሕብስቱ ላይ የፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ይሁዳ ከፈጸመው የባሰ መሆኑን የሚያረጋግጥብዎትን አላርፍ ካሉ ወደፊት ከሌሎቹ ጋር በዝርዝር ይቀርባል ፡፡ በዚያን ጊዜ የይሁዳ እጣ ይደርስዎታል ፡፡
ስለ ገንዘብ ለጠቀሱት የሴንትሉሱ ቄስ ተብዬ የታክሲ ሾፌር በመሆን ወንበዴዎቹንና በዝሙት አዳሪዎቹን አመላላሽ ሆነው ቅስናዎን ለፍላጎትዎ የሸጡ እርስዎ አይደሉምን ? አሁንም አጣርቼ እንደተረዳሁት ምንም ሳይሠሩ ሕዝቡን እያፋጁ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ዶላር እየተከፈለዎ የመድኃኔ ዓለምን ቤተ ክርስቲያን አቆርቁዘውና ሕዝቡን አብረው ውድቀት አፋፍ ላይ ያደረሱት እርስዎ አይደሉምን ? ቅዱሱ የእግዚአብሔር ቃል ያገለገሉበት እንዲከፈላቸው ባዘዘው መሠረት አባቶች ጳጳሳትና መነኮሳት በየቦታው በመዘዋወር ሕዝቡን ለቅዱስ ዓላማ ሲያደራጁና ቤተ ከርስቲያን መስርተው ለቅዱስ ዓላማ ሲያበቁ ካህናቱ ዲያቆናቱ ጭምር የተቀደሰውን አገልግሎት ሲሰጡና ሲያስተምሩ በየቤተክርስቲያኑ የእግዚአብሔር በረከት አድሮ ሕዝቡ በፈቃደኛነት የሰጣቸው ለምግብና ለኑሮአቸው የሚያውሉት ገንዘብ ማግኘት በርስዎ በሕዝብ ከፋፋዩ ያስኮንናቸዋልን ? በጣም አሳዛኝ ነው ይህን ተመልካች ሁሉ ይፍረደኝ ለአንባብያን ትቼዋለሁ ፡ ቢሆንስ ታዲያ እርስዎን ምን አስቀናዎ ? መረገም ነው ፡፡
ደግሞም ማርያም ኃጢአተኛ ነች ካልተባለኝ ሞቼ እገኛለሁ ብለው በጣር እየቃተቱ ሲቧጭሩ ይታያሉ ፡ እንደ ይሁዳ ገመድ በአንገትዎ ይክተቱ እንጂ የመድኃኒታችን የክርስቶስን እናት እመቤታቺንን ኃጢአተኛ ነች የሚል ከጀሌዎችዎና ከርስዎ በቀር ዲያብሎስ የለምና ሌላ ሰው አያገኙም ይረፉ ፡፡ አንድ ሰውዬ ለጓደኛው ማርያምን ትፈራታለህ ወይ ? ቢለው እሱም መልሶ ምነው አልፈራት ይለዋል ጠያቂውም ለምን ? ቢለው ከግንድ የሚያላጋ ልጅ አላት አለው ይባላል ፡፡ ቢያስተውሉ እርስዎን የመሰለ እኩይ ልጇና እሷ ከሚመሰገኑበት ቤቷ ውርደት አከናንቦ ነቀለላት አሁንም አላርፍ ስላሉ መድኃኔ ዓለም ከመመስገኛ ቤቱ ከግንድ እስኪያላጋዎትና እስኪነቅልዎት እየቃተቱ ይጠብቁ ፡፡
በገጽ አስራ ሰባት ጽሁፍዎ በመጨረሻው ፓራግራፍ ላይ (ዮሐንስ አፈወርቅ ፫፻፲፱፡፹፯) ማለትም በልቡ ቂም በቀል የተሞላ በተቀደሰው ቦታ አይቁም ይወገድ ይላል የሚል ጠቅሰው ጽፈዋል ፡፡ ካሁን ቀደም ባቀረብኩት ጽሁፍ የአገራችን ጸበል እንደሚያስፈልግዎና ሄደው እንዲጠመቁ ጠቁሜዎ ነበር አልተቀበሉትም መሰለኝ አገረሸብዎት ቅጥፈቱ እየባሰብዎት ሔደ ፡፡
ለመሆኑ ሕዝብ በተሰበሰበበት በመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ ቆመው አስተምራለሁ ብለው ሲቃዡ ‘’እኔ ቂም አልፍቅም’’ ያሉትንና ‘’ቂም የማትይዝ አህያ ብቻ ነች ቂም ኃጢአት አይደለም’’ ብለው ለሕዝብ ያስተማሩትን የመናፍቅ ቃል ዘንግተውት ነውን ? ሌላውን ለመኮነን ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ ብለው ያቀረቡት ? ሕዝቡን አእምሮው የማያስተውል ከብት አድርገውት ነውን ? እንግዲህ የእኔም አባባል ቅዠታም ስለሆኑ ባቀረቡት ጽሁፍ መሠረት ከተቀደሰው የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መወገድ አለብዎት የጳጳሱም እግድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከሥልጣንዎ አስወግዶዎታልና በጥብቅ ያስቡበት በማለት ቁጣው በልቡ በታመቀው ሕዝብ ስም አስጠነቅቅዎታለሁ ፡፡
በገጽ አስራ ስምንት ላይ ‘’በተለይ መነኩሴዎችን ቄሶችን ሰባኪዎችን ጳጳሳቱንና ከፍካሬ ኢየሱስ ጋር በመጋጨት ላይ ያሉትን መንፈስ ቅዱስ ወለዳቸው ልንል አንችልም’’ ሲሉ እራስዎን መንፈስ ቅዱስ እንደወለደዎ አድርገው ሁሉንም ኮነኑ ‘’ለማያውቅብሽ ታጠኝ’’የሚባለውን ዘይቤ ያውቁታል ? ሌላውን ያታሉ ሕዝቡ ከነቃብዎት ዋል አደር ብሏል ፡፡ ከባእድ አገር መጥተው ሕዝቡን ሰብስበው ስለ እምነቱ እንዲያውቅና የተበተነው ተሰባስቦ ፈጣሪውን እንዲያመሰግን የሚያደርጉት የጠቀሷቸው ጳጳሳት መነኮሳት ካህናትና ዲያቆናት መንፈስ ቅዱስ ወልዷቸውና ፈቅዶ አዟቸው መጥተው የሚያገለግሉ ሲሆን ተቃራኒያቸው እርስዎ ግን በትክክል ዲያብሎስ የወለደዎ ለመሆኑ በየሔዱበት የሚከፋፍሉት ሕዝብና ሥራዎ ምስክር ለመሆኑ በጉልህ ታውቛል ፡፡
በገጽ አስራ ዘጠኝ የጠቀሱት ጳጳሳቱንና መነኮሳቱን የኮነኑበት ሲታይ የቀጣፊ የተለምዶ አሉባልታ ወሬ እንጂ ምንኩስና ሞት ነው ላሉት ከዚህ ዓለም ኃጢአትና መጥፎ ተግባር ተወግዶ ሕዝብን ማስተማርና ለእግዚአብሔር ቤት ማገልገል መሆኑ ግልጽ ነው እንዲሁም የዚህን ከንቱ ዓለም ውንብድና እንደ ሞት ተለይተውት ሕዝቡን ከዓለማዊ ኑሮ ወደ ቅድስና እንዲመልሱ የተሾሙት ጳጳሳትና መነኮሳት እንደርስዎ ባለ ሕዝብን ከፋፋይና ለሴቶች እይታና ለዚህ ከንቱ ዓለም ውንብድና ፀጉርዎን (ሜካፕ) የቁንጅና ቀለም በመቀባት በሚቆነጃጁ ወረኛ ስም አጥፊ የሚሰደቡ አይደሉም ፡፡ ሕዝቡን ወደ ፈጣሪው ለመመለስ ከፈጣሪአቸው የተቀቡ ለመሆናቸው የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፰ እስከ ፴ ያለው ‘’በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ’’ ያላቸውን ብፁዐን አባቶች በከረፋው አንደበትዎ መዝለፍ ስርየት የሌለው ኃጢአት ነው ፡፡ እነዚህ አባቶች ባይኖሩ በሕዝቡ ላይ እንደእርስዎ ያለ ዓለማዊ አወናባጅ መናፍቅ ቄስ ነኝ ባይ ይጨፍርባቸው ነበር ፡፡
በገጽ ሃያ ላይ መነኮሳቱን ፡ ጳጳሳቱን ፡ ካህናቱን ሐሰተኞች ለማለት እንተባበር ብለው ያልሆነ ፕሮፓ ጋንዳ ከነዙ በኋላ ማዕድ ተሳታፊው ሁሉ ለቁባቶቻቸው መጋረጃ እየሆነ ነው ብለው በለመደው የቅዠት አንደበትዎ የማይመስልና አስነዋሪ የሆነ ስም ማጥፋት ሰንዝረዋል ፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ሕዝቡ ተባብሮ በመነሳት ማጥፋት ያለበት እንደ እርስዎ ያለውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሴቶች እያፈራረቀ የሚያሳድረውንና ሚስትን ከባሏ ለይቶ ባለሟል ጓደኛ የሚያደርገውን እንዲሁም እንደ ሴቶች የፀጉር ቀለም የሚቀባውን ባለጌ ቄስ ነኝ ባይ ነው እንጂ የተከበሩትን ጳጳሳትና መነኮሳት አይደለም መልካሙ ሥራቸው ይመሰክራል ፡፡
ለመሆኑ እርስዎ አብረው ተቀምጠው አላዩ በዐይንዎ ያላዩትን እንዳየ ሰው ሆነው በውሸት ስም ማጥፋት የቄስ ተግባር አይደለም ቄስ የሰውን ንስሐ ጠባቂ እንጂ እንደ እርስዎ ቀጣፊ አሉባልተኛ አይደለም ይህ እግዚአብሔር ይቅር የማይለው ኃጢአት ነውና የፈጸሙት ጠቅላላ አስነዋሪ ተግባርዎ ወደፊት በዝርዝር ሲገለጽብዎ እንደ ይሁዳ መሸሸጊያ ሲጠፋብዎ ይታየኛል ፡ ሕዝቡ አላወቀብኝም ብለው ንጹህ በመምሰል እባክዎን አይዘላብዱ ፡፡
አባቶቻቺን ብፁአን ጳጳሳትና መነኮሳት እንደ እርስዎ በመጥፎ አስነዋሪ ነገር ስማቸው ተነስቶ አያውቅም እንደ እርስዎ ያለው ስም አጥፊ መናፍቅ ግን ያላየውን ውሸት በመዘላበዱ በሰው ዘንድ ተጠልቶ ዐይንህ ለአፈር እየተባለ መሸሸጊያ ጠፍቶታል ፡
አባቶቻቺንም ሆኑ ካህናቱ እንዲሁም ዲያቆናቱ በእውቀት ስለሚበልጥዎት አጸፋውን መልስ መስጠት አቅቷቸው ሳይሆን ‘’ለበሬ ፈስ አፍንጫ አይያዝለትም’’ እንደሚባለው ምንጊዜም ሰይጣን እንደሚፈታተናቸው ስለሚያውቁ ይህን ቀንደኛ ዲያቢሎስ በዝምታ ድል ነስተውታል ፡፡
እኛም እግዚአብሔር ይገስጽልን እንላለን ፡፡ አሜን ፡፡
No comments:
Post a Comment